Tuesday, March 14, 2023

አለም አቀፉ የሴቶች ቀን በድምቀት ተከበረ ::

ቀን 5/7/2015 .

 

አለም አቀፉ የሴቶች ቀን በድምቀት ተከበረ ::

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አለም አቀፉን የሴቶች ቀን(march 8) እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ በሚል መሪ ቃል አጠቃላይ የቢሮው ሰራተኞች በተገኙበት አከበረ።

 

ቀኑ ዘንድሮ በሀግራችን 47 እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 112 ጊዜ እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ እንደሚገኝ የቢሮው የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ዘውዴ ገልጸው ቀኑ በሀገራችን መከበር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የሴቶች እኩልነት ህገመንግስታዊ ዋስትና እንዲያገኝ ከማስቻሉ ባሻገር በተለያዩ የልማት መስኮች የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ቀኑን ማክበር የሚያስፈልገው ለሴቶች የሚገባቸውን ክብር እና በተለያዩ መስኮች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ተገቢውን እውቅና በመስጠት መሆኑን ጠቁመው በትምህርት ዘርፉ የሴቶች ተሳትፎም ሆነ ውጤታማነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተ እድገት እያሳየ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

 

አለም አቀፉ የሴቶች ቀን ተከብሮ የሚውልበት ዋነኛ አላማ በሴቶች ትግል የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል ለሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግን ታሳቢ አድርጎ እንደመሆኑ በሁሉም ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ የቢሮው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ አስገንዝበዋል።

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

Ticktack- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

 

No comments:

Post a Comment