Wednesday, March 8, 2023

 

ቀን 29/6/2015 .

 

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማትምህርት ማህበረሰቡ ጋር በድምቀት ተከበረ፡፡

 

በአለም አቀፍ ደረጃ 112 ጊዜ በኢትዮጵያ ደረጃ ደግሞ 47 ጊዜ ‹‹ እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ›› በሚል መሪ ቃል 2015 . የሴቶች ቀንን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት /ቤት አዘጋጅነት ሴት ርዕሰ መምህራን፣ ሴት ሱፐርቫይዘሮች፣ ሴት ዲፓርትመንት ተጠሪዎች፣ የስርዓተ ጾታ ክበብ ተጠሪ መምህራንና አባል ተማሪዎች፣ መጋቢ እናቶች፣ ሴት ቡድን መሪዎች፣ ሴት የትምህርት ባለሙያዎች እና የክፍለ ከተማው ሴት መምህራን ማህበር በተገኙበት በድምቀት የተከበረ ሲሆን በእለቱም ሴት ርዕሰ መምህርት እና ሴት ሱፐርቫይዘር የህይወት ተሞክሮአቸውን ለታዳሚዎች በማካፈል ተማሪዎች የተለያዩ ስነ-ጽሁፎችና ውዝዋዜዎችን በማቅረብ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

 

ጠንካራ ሰራተኛ እና ጠንካራ መሪ ለመሆን ጠንክሮ መስራትና በየደረጃው ያለውን ኃላፊነት በመቀበል አርአያ ሆኖ መገኘትና ሴት ተማሪዎቻችንን ቀርበን ድጋፍ በመስጠት ውጤታማ ተማሪዎች እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት /ቤት ኃላፊ ሳምራዊት ቅባቱ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ለተማሪ ነጂባ አማን ሽልማት በመሰጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

No comments:

Post a Comment