Tuesday, March 7, 2023

በአዲስ አበባ ከተማ የተማሪዎች ውጤትን ለማሻሻል የሚያስችል የዋንጫ ርክክብ ተካሄደ።

 

ቀን 28/6/2015 .

 

በአዲስ አበባ ከተማ የተማሪዎች ውጤትን ለማሻሻል የሚያስችል የዋንጫ ርክክብ ተካሄደ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ ከተማ አቀፍ እና ሀገራቀፍ ፈተና ተፈታኝ የሆ ኑ የ6ኛ ፣የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት የላቀ እንዲሆን እና ተማሪዎች በፍክክር መንፈስ የተሻለ ውጤት መስመዝገብ እንዲችሉ የተማሪዎች ውጤት ማሻሻያ የዋንጫ ርክክብ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄዳል፡፡

 

ዋንጫው ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት /ቤት ርክክብ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በሁሉም ክፍለከተሞችና በሁሉም ትምህርት ቤቶች  የሚዘዋወር ይሆናል።

 

ዋንጫው 6 8 እና 12 ክፍል ሀገር አቀፍና ከተማ አቀፍ ፈተናዎች ላይ የሚኖረውን ውጤት ለማሻሻል እንዲቻል በተማሪዎች ላይ መነቃቃትንና የውድድር መንፈስን ለማሳደግ  ትኩረት ተሰጦ የሚሰራበት ነው።

 

መድረኩ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዘጋጅነት በፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጀመረ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል ፣ የቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊ ሳምራዊት ቅባቱ ፣ ርዕሳነ መምህራን ፣ ባለሙያዎች ፣ ወላጆች ፣ መምህራን እና ተማሪዎች ተሳታፊ ሁነዋል፡፡

 

በመድረኩ በ2015 የትምህርት ዘመን ከተማ አቀፍ እና ሀገራቀፍ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በፍክክር መንፈስ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ በሶስቱም የክፍል ደረጃዎች ላይ ተማሪዎች ተግተው እንዲሰሩ እንደሚያደርግ የተመላከተ ሲሆን በዓመቱ መጨረሺያ ላይ ዋንጫዎቹ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ላሉባቸው ክፍለ ከተማዎች የሚበረከቱ እንደሚሆኑ ተገልጻል፡፡

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

No comments:

Post a Comment