Friday, March 10, 2023

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 አከበረ፡፡

 

ቀን 1/7/2015 .

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 አከበረ፡፡

 

በበአሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የሴት አመራሮች ህብረት ወ/ሮ ደብሪቱ ጌታቸው  የሴት መምህራን ትውልድን የመቅረፅ ሚና ከፍተኛ መሆኑን  ጠቁመው፤ መምህራን በአሉን ከማክበር ባለፈ ለራሳችንንና ለሴት ተማሪዎች አቅም ለመፍጠር በብቃት መስራት አለብን ብለዋል ፡፡

 

የመምህራን ማህበሩ ስርዓተ ጾታ ክፍል የመጡት ወ/ሮ እየሩስ ብዙነህ እንዳሉት የዘንድሮውን ማርች 8 የሴቶች ቀን ሲከበር የሚመለከታቸው አካላትን በማስተባበር በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ያሉ ሴት ተማሪዎች   የንፅህና መጠበቂያ መጠቀም እንዲችሉና በየትምህርት ቤቱ ያሉ ሴት ተማሪዎች የሱስ ተጠቂ እንዳይሆኑ በትምህርት ማህበረሰቡ የውህደት መድረክ እንቅስቃሴ እንዲፈጠርና የማካተት ስራዎች እንዲሰሩ ጥረት እንደሚደረግ   አብራርተዋል፡፡

 

በእለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የግብርና ሚኒስቴር አማካሪ ወ/ሮ ሰአዳ በንግግራቸው በሴቶች ላይ የተፈጠሩ ተፅዕኖዎችን ብቻ ሳይሆን መልካም ውጤት ያመጡ ሴቶችንም  ማጉላት  እንደሚገባ ተናግረው፤ በአለምቀፍ ተፅእኖ ፈጣሪ የሆኑ ሴቶችን ተሞክሮ አቅርበዋል፡፡

 

ማርች 8 አለምአቀፍ የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ለ47ኛ ፤ በአለም ለ112 ኛ ጊዜ እየተከበረ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ፡፡ 

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

No comments:

Post a Comment