ቀን 22/6/2015
ዓ.ም
የአዲስ
አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት በትምህርት ተቋማት ሲያካሂድ የቆየውን የ2015 ዓ.ም የ6ወር የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘና በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡
ምዘናው
በሁሉም የመንግስት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጨምሮ በክፍለከተማ እና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች አስሩን ዋና ዋና ግቦች መነሻ በማድረግ የተካሄደ ሲሆን ቀደም ሲል ምዘናውን ለሚያካሂዱ ከ400 በላይ ለሚሆኑ መዛኞችና አስተባባሪዎች ኦረንቴሽን መሰጠቱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ጌታሁን ለማ ገልጸዋል፡፡
በትምህርት
ተቋማት የሚካሄደው የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘና ተቋማቱ ያሉበትን ሁኔታ በማወቅ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ከማስቻሉ ባሻገር በተቋማቱ መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት
እንዲችሉ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመው ምዘናው ያለምንም እንከን እንዲካሄድ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ መዛኞችና ተመዛኝ
ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
Blog: - https://aacaebc.blogspot.com
You
Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
No comments:
Post a Comment