Friday, March 3, 2023

በተሻሻለው የስርዓተ ጾታ መመሪያ እና ተዛማጅ ጉዳዮች

 

ቀን 24/6/2015 .

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት በተሻሻለው የስርዓተ ጾታ መመሪያ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን አሳወቀ።

 

በስልጠናው የክፍለ ከተማ የዘርፈ ብዙ ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የስነ ዜጋና ስነምግባር መምህራን እና የጋይዳንስና ካውንስሊንግ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

 

በስልጠናው መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ዘውዴ እንዳስታወቁት የስርዓተ ጾታ መመሪያው 2007 . በኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስተር ተዘጋጅቶ በየትምህርት ተቋማቱ ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመው መመሪያው ዳግም በአዲስ መልክ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ አድርጎ በመዘጋጀቱ በዚህ የአሰልጣ ኞች ስልጠና ተሳታፊ የሆኑ መምህራንም ሆኑ የትምህርት ባለሙያዎች በየትምህርት ቤቶቻቸው መመሪያውን መሰረት በማድረግ ለትምህርት ማህበረሰቡ ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ባለሙያ አቶ ደረጀ ደምሴ በመርሀ ግብሩ ጾታዊ ጥቃትንም ሆነ በህጻናት ላይ የሚደርሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል የወጡ አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የህግ ማእቀፎችን መሰረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ሰልጣኞቹም በቀረቡ የመወያያ ሀሳቦች ዙሪያ በቡድንና በጋራ ውይይት አድርገዋል።

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

No comments:

Post a Comment