ቀን 14/7/2015 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ6ወር የቢ ኤስ ሲ አፈጻጸም ምዘና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅና ሰጠ።
እውቅናው ለትምህርት ቤቶች፣ወረዳና ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶን ጨምሮ በቢሮ ለሚገ ኙ ስራ ክፍሎች እና በአጋርነት ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት የተሰጠ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች፣መምህራን ፣ርዕሳነ መምህራን እንዲሁም የመምህራን እና የተማሪ ወላጅ ማህበር ተወካዮች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በእውቅና መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የምዘና ስርአቱ ሳይንሳዊ እና ፍትሀዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበው የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ አዲሱ ስርአተ ትምህርት ተግባራዊ የተደረገበት መሆኑ የዘንድሮውን ምዘና ለየት እንደሚያደርገው በመግለጽ በቀጣይ 6 ወራት ውጤታማ ሆነው የተሸለሙ ተቋማት ለሌሎች ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉበት እና በአፈጻጸማቸው ዝቅተኛ የሆኑት ደግሞ ለተሻለ ውጤት የሚተጉበት ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው ምዘናው የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ መካሄዱን ጠቁመው ምዘናውም በዋናነት በተቋማቱ መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር ተቀራራቢ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ታስቦ የሚካሄድ መሆኑን አስረድተዋል።
የ2015ዓ.ም የ6ወር የቢ ኤስ ሲ አፈጻጸም ምዘና ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የምዘና መስፈርት ከማዘጋጀት ጀምሮ ለመዛኞች ኦረንቴሽን ተሰጥቶ ወደ ምዘና መገባቱን የትምህርት ቢሮ የእቅድና በጀት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የምዘና ሂደቱን በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸው ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት በተካሄደው ምዘና 469 ተቋማት በ590 መዛ ኞች ተመዝነው ለዛሬው የእውቅና መርሀ ግብር መብቃታቸውን አስታውቀዋል።
በምዘናው ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1ኛ አጼ ቴውድሮስ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ 2 ኛ ረጲ ከኮልፌ ክፍለ ከተማ እንዲሁም 3ኛ ልቤፋና ትምህርት ቤት ከቂርቆስ ክፍለከተማ በመሆን እውቅና ሲሰጣቸው ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በቢ ኤስ ሲ እና በ12ኛ ክፍል ውጤት 1ኛ አዲስ ከተማ 2ኛ በሻሌ እንዲሁም ቦሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 3ኛ በመውጣት እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን በቢኤስ ሲ አፈጻጸም ብቻ ደግሞ 1ኛ በላይ ዘለቀ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 2ኛ በሪ 2ኛ ደረጃ እንዲሁም ቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 3ኛ በመሆን ተሸልመዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
No comments:
Post a Comment