Tuesday, March 14, 2023

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምራል፡፡

 

ቀን 5/7/2015 .

 

አዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 2 ዓመት የስራ ዘመን 3 መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምራል፡፡

 

ምክርቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 2015 ዓም የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት  ላይ ይወያያል፣ ረቂቅ  ማሻሻያ አዋጅ ላይ  ተወያይቶ ማጽደቅና  ሌሎች አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ ይጠበቃል።

 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 ዓም የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት  ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርታቸዉ ፡- የፀረ-ሌብነት ትግልን በማጠናከር፡ የህግ በላይነት የማስከበር፣ የተጠያቂነት ለማስፈን በሕዝባዊ ንቅናቄ የተደገፉ ስራ እየተሰራ ነው፡፡ የፀረ-ሙስና እና ስነ- ምግባር ኮሚሽን በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ስራ ጀምሮአል:: በከተማ ደረጃ የፀረ ሙስና ንቅናቄ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ከህብረተሰቡ ጥቆማ በመቀበል  215 አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ደላሎች በህግ ቁጥጥር ስር ሆነው ጉዳያቸው በፍትህ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

ይሄም በዝርዝር ሲታይ የካ /ከተማ 40 ንፋስ ስልክ ላፍቶ 42  ለሚ ኩራ 48 ልደታ 26 አቃቂ ቃሊቲ 33 በማዕከልና ሴክተሮች 26 የሚሆኑ በህግ ተጠያቂ ሆነዋል፡፡

 

በተጨማሪም ከማዕከል አስከ ወረዳ ባሉ ተቋማት 3,584 አመራርና ሰራተኞች በተለያዩ የዲሲፕሊን ግድፈቶች አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተደርጓል ያሉ ሲሆን፡፡

 

ባለፉት 6 ወራት የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቅለል የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎችን በተመለከተ :-

 

  የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት በተሰራው ስራ፤ 170,128 የሰብል ምርት በገበያ ማዕከላት ትስስር መፍጠር ተችሏል፡፡

 

  የእሁድ ገበያ(Sunday Market) በሁሉም /ከተሞች 137 የገበያ መዳረሻዎች በማስፋፋት የግብርና ምርቶች ከአርሶ አደሩ ወደ ተጠቃሚው በቀጥታ እንዲደርሱ በማድረግ ሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን እንዲያገኝ እየተደረገ ይገኛል

 

  የመሠረታዊ ፍጆታ ሸቀጦች አቅርቦት ለህብረትሰቡ በፍትሃዊነት ተደራሽ ከማድረግ አንፃር 272,777 ስኳር ማሰራጨት ተችሏል።

 

  10.9  ሚሊዮን ሊትር ፓልም ዘይት ማሰራጨት ተችሏል

 

  194 ሚሊዮን የሸገር ዳቦ በሸገር ዳቦ በመሽጫ ሱቆች ማሰራጨት ተችሏል

 

  ከሸገር የዳቦ ፋብሪካ በተጨማሪ የተገነቡት የዳቦ ፋብሪካዎች ቁጥር 25 ማድረስ ተችሏል

 

  የከተማ አስተዳደሩ በመደበው 1.4 ቢሊዮን የተዘዋዋሪ ብድር በመጠቀም በድምሩ 356,761 ኩንታል ጤፍ በሸማች ኅብረት ሥራ ማህበራት በኩል በማቅረብ ገበያ የማረጋጋት ስራ ተሰርቷል

 

  ለትምህርት ቤት ምገባ የወቅቱን ኑሮ ውድነት መነሻ በማድረግ በዓመት ተጨማሪ 54 ሚሊዮን ብር ተመድቦ የመጋቢ እናቶችን ጫና የመቀነስ እና የተማሪዎችን ምገባ የተሻለ ለማድረግ የሚያስችል ስራ ተሰርቷል

 

  በዘላቂነት የኑሮ ውድነት ጫና  ለመቀነስና ገበያን ለማረጋጋት በአዲስ አበባ የመግቢያ በሮች ማለትም በኮልፌ በንፋስልክ ላፍቶ በለሚ ኩራ እና በአቃቂ ክፍለ ከተሞች አራት ትላልቅ ሁለገብ የግብርና ምርቶች ማከፋፈያ ማዕከላት ግንባታ በዚህ በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ 24 ሰዓታት እየተሰራ ይገኛል

 

. የሌማት ትሩፋት ስራችን አዲስ የልማት ከፍታ ጉዞ በሚል ከጥቅምት 27 ጀምሮ 52,228 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በተለይ የወተት፣ የዶሮ ስጋ እንቁላል እና የማር ምርታማነት በማሳደግ እንዲሁም የጓሮ አትክልት በማምረት ያለንን አቅም እና ጸጋ ወደ ተግባር በመቀየር የከተማችንን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና ለማቅለል እየተሰራ ይገኛል

 

. በከተማችን በቀን አንድ ግዜ መመገብ ለማይችሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ ነዋሪዎች 15 የምገባ ማዕከላት 30ሺህ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ተችላል ብለዋል::

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

Ticktack- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

 

No comments:

Post a Comment