Thursday, March 16, 2023

በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የትምህርት ብርሀን ምዘና አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

 

ቀን 7/7/2015 .

 

በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የትምህርት ብርሀን ምዘና አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራ እና አጠቃላይ ሱፐር ቪዝን ዳይሬክቶሬት 2015 . የትምህርት ብርሀን ምዘና አተገባበር ዙሪያ ከክፍለከተማና ወረዳ የአፋን ኦሮሞ የጎልማሶች ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

 

የትምህርት ብርሀን ምዘናው በአዲስ አበባ ከተማ 2013 እና 2014. በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ለሁለት ዙር ተካሂዶ 2,000 በላይ ጎልማሶችና ወጣቶች  50% እና ከዚያ በላይ አምጥተው የእውቅና የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራ እና አጠቃላይ ሱፐር ቪዝን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሮቢ ዋሚ አስታውቀዋል፡፡

 

ዳይሬክተሩ አክለውም የዘንድሮው የትምህርት ብርሀን ምዘና ከመጋቢት 11/2015 . ጀምሮ እስከ መጋቢት 30/2015 . ድረስ በሁሉም የጎልማሶች ትምህርት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ጠቁመው በዚህ አመት ከዚህ በፊት ከነበረው የተሻለ ቁጥር ያላቸው ጎልማሶችና ወጣቶችን በአፋን ኦሮሞ  ቋንቋ  በመመዘን ደረጃውን የጠበቀ የእውቅና የምስክር ወረቀት ለመስጠት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱን አስገንዝበዋል፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት  የጎልማሶች ትምህርት ባለሙያው አቶ ጌታቸው በላይነህ በበኩላቸው የትምህርት ብርሀን ምዘናው የማንበብ መጻፍና ማስላት ክህሎቶችን መሰረት አድርጎ እንደሚሰጥ እና 50% እና ከዚያ በላይ የሚያስመዘግቡ ተመዛኞች በመደበኛው ትምህርት 2 ክፍል ካጠናቀቁ ተማሪዎች ጋር አቻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸው አስታውቀዋል፡፡

 

ምዘና ወስደው የሚፈለገውን ማለፊያ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተመዛኞች በመደበኛ ትምህርት 3 ክፍል ገብተው መማር የሚችሉበት እድል ከመመቻቸቱ ባሻገር የተለያዩ የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ገልጸው በምዘናው 50% በታች የሚያስመዘግቡ ጎልማሶችና ወጣቶች በድጋሜ ምዘናውን የሚወስዱበት መንገድ መመቻቸቱንም አስረድተዋል፡፡

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

Ticktack- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

No comments:

Post a Comment