Wednesday, March 1, 2023

ለተማሪዎቻችን ምግብ ብቻ ሳይሆን ፍቅርንም እየሰጠን ሃገሩን የሚወድ ጠንካራ ዜጋ የማፍራት ስራችንን እንቀጥላለን፡-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

ቀን 22/6/2015 .

 

ለተማሪዎቻችን ምግብ ብቻ ሳይሆን ፍቅርንም እየሰጠን ሃገሩን የሚወድ ጠንካራ ዜጋ የማፍራት ስራችንን እንቀጥላለን፡-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

8ኛው የአፍሪካ የትምህርት ምገባ ቀንን የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የትምህርት ሚኒስትሮች የዓለም የምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የትምህርት ኮሚሽነሮች እንዲሁም የተለያዩ ሃገራት የምገባ ኤጀንሲዎች በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ መከበሩን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ / አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል::

 

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ትላንት ስንጀምረው ቀላል ይመስል የነበረው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ዛሬ ላይ አድጎ እና አለምአቀፍ እውቅናን አግኝቶ የተለያዩ ሃገራት ልምድ የሚወስዱበት ስራ በመሆኑ እጅግ ደስ ይለናል ብለዋል::

 

አሁንም ትውልድ የመገንባት ስራችን በማጠናከር "ለተማሪዎቻችን ምግብ ብቻ ሳይሆን ፍቅርንም እየሰጠን ሃገሩን የሚወድ ጠንካራ ዜጋ የማፍራት ስራችንን እንቀጥላለን "ሲሉም አስታውቀዋል::

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

No comments:

Post a Comment