Tuesday, February 28, 2023

የ8ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በዓል ተሳታፊ የሆኑት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብ...

የነጻ የዉጭ ሀገር የትምህርት እድል ያገኙ ተማሪዎች

273 ተማሪዎች ሙሉ የውጭ ሃገር ነፃ የትምህርት...

የ"አፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀንን"

 

ቀን 21/6/2015 .

 

"አፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀንን" በከተማችን ለማክበር ለመጡ የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) መሪዎች፣ ለአፍሪካ የትምህርት ሚኒስትሮች፣ ለዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በተጨማሪም ለተለያዩ አገራት አምባሳደሮች የተስፋ ብርሀን እና የመቅደላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምገባ ማዕከላችንን ልምድ አካፍለናል።

 

ይህን በጎ ተግባር ስንጀምር በውስጣችን ያለውን አቅም ተማምነን ነበር በዚህም እኛው ለእኛው የለውጥ ብርሀን መሆን እንደምንችል አሳይተን የሰራነው መልካም ስራ ፍሬ በማፍራቱ የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀንን በከተማችን ለማክበር  እና ከእኛ ልምድ ለመቅሰም ከተማችንን መርጠዋል።

 

 

የጀመርነው መንገድ ቀና ነውና የህዝባችንን የኑሮ ሸክም ለማቅለል እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በትጋት  መስራታችንን እንቀጥላለን።

 

 

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

የመምህራንን ስፖርታዊ ውድድር በድምቀት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ፡፡

 

ቀን 21/6/2015 .

 

2015 . የተማሪዎችና የመምህራንን ስፖርታዊ ውድድር በድምቀት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ፡፡

 

በሰፖርታዊ ውድድሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስአበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ጋር በጋራ በመሆን የሚያካሂድ ሲሆን እስካሁን ውድድሩን ለማካሄድ በተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ዙሪያ  ከሶስቱ ተቋማት የተውጣጡ አመራሮች ውይይት አካሂደዋል፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በውይይቱ እንዳስታወቁት በከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ኮቪድን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይካሄዱ መቆየታቸውን ጠቁመው ውድድሩ በዋናነት ከመደበኛው የመማር ማስተማር ተግባሩ ባሻገር በተማሪዎችና መምህራን መካከል የርስ በርስ ወዳጅነትን የሚያዳብር ተግባር በመሆኑ ትምህርት ቢሮ የዘንድሮው ውድድር በድምቀት እንዲካሄድ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ለውድድሩ ውጤታማነት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንደሚወጣ አስገንዝበዋል፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ይፍሩ በበኩላቸው ትምህርት ቤቶች ተተኪ ስፖርተኞች ከሚፈሩባቸው ተቋማት  መካከል ግንባር ቀደሞቹ እንደመሆናቸው በከተማ አስተዳደሩ በመምህራንም ሆነ በተማሪዎች መካከል የሚካሄደው ስፖርታዊ ወድድር የሚፈለገውን አላማ እንዲያሳካ ከመወዳደሪያ ስፍራ ዝግጅት ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው ወድድሮቹም በእግር ካስ ፤ቮሊቮል ፤ጠረጴሳ ቴኒስ እንዲሁም በቼዝ እና ዳርት እንደሚካሄዱ አስረድተዋል፡፡

 

በመምህራን መካከል  የሚካሄደው  ውድድር 5 ጊዜ የተጠናከረ የመምህራን ህብረት ለከተማችን ሰላምና ለትምህርት ጥራት በሚል መሪቃል ከየካቲት 25 እስከ መጋቢት 24/2015 . እንዲሁም የተማሪዎች ውድድር ደግሞ ዘንድሮ 9 ጊዜ በስፖርት የተገነባ ጤናማ ዜጋ በመፍጠር የትምህርት ጥራትን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 24 እስከ ሚያዚያ 14/2015 . ድረስ በድምቀት እንደሚካሄድ  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስፖርት ትምህርት ዝግጅት ባለሙያው አቶ ተስፋዬ አቤ አስታውቀዋል፡፡

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

Monday, February 27, 2023

Experiment in transpiration

የ6 ወር የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘናን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀመረ

 

ቀን 20/6/2015 .

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት 2015 . 6 ወር የቢ ኤስ እቅድ አፈጻጸም ምዘናን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀመረ፡፡

 

ምዘናው እስከ 2014 . ድረስ በለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካይነነት ሲካሄድ ቆይቶ ዘንድሮ በእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እንዲመራ በተወሰነው መሰረት ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ትምህርት ቢሮ ድረስ አስሩን ዋና ዋና ግቦች መነሻ በማድረግ የሚካሄድ ሲሆን  ቀደም ሲል 400 በላይ ለሚሆኑ መዛኞችና አስተባባሪዎች በምዘናው ሂደትና ለመመዘኛነት በተዘጋጁ መስፈርቶች ዙሪያ ኦረንቴስን መሰጠቱ  ይታወቃል፡፡ 

 

ምዘናው በዛሬው እለት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተጀመረ መሆኑን እና ከነገ ጀምሮ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የወረዳና ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እንደሚመዘኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ ገልጸው በትምህርት ተቋማት የሚካሄድ የቢ ኤስ እቅድ አፈጻጸም ምዘና ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ከማስቻሉ ባሻገር በተቋማቱ መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት  እንደሚያስችል አስታውቀዋል፡፡

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/