ቀን 20/6/2015
ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም የ6 ወር የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘናን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀመረ፡፡
ምዘናው እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ በለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካይነነት ሲካሄድ ቆይቶ ዘንድሮ በእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እንዲመራ በተወሰነው መሰረት ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ትምህርት ቢሮ ድረስ አስሩን ዋና ዋና ግቦች መነሻ በማድረግ የሚካሄድ ሲሆን ቀደም ሲል ከ400 በላይ ለሚሆኑ መዛኞችና አስተባባሪዎች በምዘናው ሂደትና ለመመዘኛነት በተዘጋጁ መስፈርቶች ዙሪያ ኦረንቴስን መሰጠቱ ይታወቃል፡፡
ምዘናው በዛሬው እለት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተጀመረ መሆኑን እና ከነገ ጀምሮ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የወረዳና ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እንደሚመዘኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ ገልጸው በትምህርት ተቋማት የሚካሄድ የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘና ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ከማስቻሉ ባሻገር በተቋማቱ መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚያስችል አስታውቀዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
Blog: - https://aacaebc.blogspot.com
You
Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
No comments:
Post a Comment