Tuesday, February 28, 2023

የመምህራንን ስፖርታዊ ውድድር በድምቀት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ፡፡

 

ቀን 21/6/2015 .

 

2015 . የተማሪዎችና የመምህራንን ስፖርታዊ ውድድር በድምቀት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ፡፡

 

በሰፖርታዊ ውድድሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስአበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ጋር በጋራ በመሆን የሚያካሂድ ሲሆን እስካሁን ውድድሩን ለማካሄድ በተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ዙሪያ  ከሶስቱ ተቋማት የተውጣጡ አመራሮች ውይይት አካሂደዋል፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በውይይቱ እንዳስታወቁት በከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ኮቪድን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይካሄዱ መቆየታቸውን ጠቁመው ውድድሩ በዋናነት ከመደበኛው የመማር ማስተማር ተግባሩ ባሻገር በተማሪዎችና መምህራን መካከል የርስ በርስ ወዳጅነትን የሚያዳብር ተግባር በመሆኑ ትምህርት ቢሮ የዘንድሮው ውድድር በድምቀት እንዲካሄድ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ለውድድሩ ውጤታማነት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንደሚወጣ አስገንዝበዋል፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ይፍሩ በበኩላቸው ትምህርት ቤቶች ተተኪ ስፖርተኞች ከሚፈሩባቸው ተቋማት  መካከል ግንባር ቀደሞቹ እንደመሆናቸው በከተማ አስተዳደሩ በመምህራንም ሆነ በተማሪዎች መካከል የሚካሄደው ስፖርታዊ ወድድር የሚፈለገውን አላማ እንዲያሳካ ከመወዳደሪያ ስፍራ ዝግጅት ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው ወድድሮቹም በእግር ካስ ፤ቮሊቮል ፤ጠረጴሳ ቴኒስ እንዲሁም በቼዝ እና ዳርት እንደሚካሄዱ አስረድተዋል፡፡

 

በመምህራን መካከል  የሚካሄደው  ውድድር 5 ጊዜ የተጠናከረ የመምህራን ህብረት ለከተማችን ሰላምና ለትምህርት ጥራት በሚል መሪቃል ከየካቲት 25 እስከ መጋቢት 24/2015 . እንዲሁም የተማሪዎች ውድድር ደግሞ ዘንድሮ 9 ጊዜ በስፖርት የተገነባ ጤናማ ዜጋ በመፍጠር የትምህርት ጥራትን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 24 እስከ ሚያዚያ 14/2015 . ድረስ በድምቀት እንደሚካሄድ  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስፖርት ትምህርት ዝግጅት ባለሙያው አቶ ተስፋዬ አቤ አስታውቀዋል፡፡

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

No comments:

Post a Comment