Tuesday, February 28, 2023

የ"አፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀንን"

 

ቀን 21/6/2015 .

 

"አፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀንን" በከተማችን ለማክበር ለመጡ የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) መሪዎች፣ ለአፍሪካ የትምህርት ሚኒስትሮች፣ ለዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በተጨማሪም ለተለያዩ አገራት አምባሳደሮች የተስፋ ብርሀን እና የመቅደላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምገባ ማዕከላችንን ልምድ አካፍለናል።

 

ይህን በጎ ተግባር ስንጀምር በውስጣችን ያለውን አቅም ተማምነን ነበር በዚህም እኛው ለእኛው የለውጥ ብርሀን መሆን እንደምንችል አሳይተን የሰራነው መልካም ስራ ፍሬ በማፍራቱ የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀንን በከተማችን ለማክበር  እና ከእኛ ልምድ ለመቅሰም ከተማችንን መርጠዋል።

 

 

የጀመርነው መንገድ ቀና ነውና የህዝባችንን የኑሮ ሸክም ለማቅለል እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በትጋት  መስራታችንን እንቀጥላለን።

 

 

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

No comments:

Post a Comment