Tuesday, March 14, 2023

በትምህርት ብርሀን ምዘና አተገባበር ዙሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

 

ቀን 5/7/2015 .

 

በትምህርት ብርሀን ምዘና አተገባበር ዙሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት 2015 . የትምህርት ብርሀን ምዘና አተገባበር ዙሪያ ከክፍለከተማና ወረዳ የጎልማሶች ትምህርት ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

 

የትምህርት ብርሀን ምዘናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዚህ በፊት ለሁለት ዙር መካሄዱን እና በዚህ ሂደትም 17,216 ጎልማሶችና ወጣቶች ምዘናውን ወስደው 13,511 የሚሆኑት 50% እና ከዚያ በላይ ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ አስታውቀዋል፡፡

 

ዳይሬክተሩ አክለውም የዘንድሮው የትምህርት ብርሀን ምዘና ከመጋቢት 11/2015 . ጀምሮ እስከ መጋቢት 30/2015. ድረስ በሁሉም የጎልማሶች ትምህርት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ጠቁመው ዘንድሮ 17,000 የሚሆኑ ጎልማሶችና ወጣቶችን 50% ከዛ በላይ እንዲያመጡ ለማስቻል ቢሮው ግብ ማስቀመጡንም አስገንዝበዋል፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የጎልማሶች ትምህርት ባለሙያው አቶ ልኡል መርጋ በበኩላቸው 2015. የትምህርት ብርሀን ምዘና ሂደቱ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው ምዘናው የማንበብ መጻፍና ማስላት ክህሎቶችን መሰረት አድርጎ እንደሚሰጥ እና 50% እና ከዚያ በላይ የሚያስመዘግቡ ተመዛኞች በመደበኛው ትምህርት 2 ክፍል ካጠናቀቁ ተማሪዎች ጋር አቻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸው አስታውቀዋል፡፡

 

ምዘና ወስደው የሚፈለገውን ማለፊያ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተመዛኞች በመደበኛ ትምህርት 3 ክፍል ገብተው መማር የሚችሉበት እድል መመቻቸቱን እና በምዘናው 50% በታች የሚያስመዘግቡ ጎልማሶችና ወጣቶች በድጋሜ እንደሚመዘኑ አቶ ልኡል አስረድተዋል፡፡

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

Ticktack- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

No comments:

Post a Comment