Sunday, March 26, 2023

የልምድ ልውውጥ በየካ ክፍለ ከተማ በብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት

 

ቀን 17/7/2015 ዓ.ም

 

የልምድ ልውውጥ  በየካ ክፍለ ከተማ በብሩህ ተስፋ የመ///ቤት

 

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የደጃዝማች ሀይሉ ተሥፋዬ ቅድመ  መጀመሪያ  ደረጃ /ቤት መምህራን በየካ ክፍለ ከተማ በብሩህ ተሥፋ ቅድመ አንደኛ ደረጃ /ቤት በመገኘት  የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል፡፡

 

የአዲሱን  ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራን በተመለከተ የዕቅድ አስተቃቀድ እንዲሁም ፣ህጻናት በተቀናጀ የህፃናት አሥተዳደግና ትምህርት በጨዋታ ፣ በመዝሙር ፣ በተግባር ሥራ እና በተረት መማር  የህጻናት ተከታታይ ምዘናን እና አጠቃላይ መማር ማሥተማር ሂደት ላይ የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል::

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

Thursday, March 23, 2023

የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ6ወር የቢ ኤስ ሲ አፈጻጸም ምዘና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅና

 

ቀን 14/7/2015 ዓ.ም

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 2015. የትምህርት ዘመን 6ወር የቢ ኤስ አፈጻጸም ምዘና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅና ሰጠ።

 

እውቅናው ለትምህርት ቤቶች፣ወረዳና ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶን ጨምሮ በቢሮ ለሚገ ስራ ክፍሎች እና በአጋርነት ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት የተሰጠ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች፣መምህራን ፣ርዕሳነ መምህራን እንዲሁም የመምህራን እና የተማሪ ወላጅ ማህበር ተወካዮች ተገኝተዋል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በእውቅና መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የምዘና ስርአቱ ሳይንሳዊ እና ፍትሀዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበው 2015 . የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ አዲሱ ስርአተ ትምህርት ተግባራዊ የተደረገበት መሆኑ የዘንድሮውን ምዘና ለየት እንደሚያደርገው በመግለጽ በቀጣይ 6 ወራት ውጤታማ ሆነው የተሸለሙ ተቋማት ለሌሎች ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉበት እና በአፈጻጸማቸው ዝቅተኛ የሆኑት ደግሞ ለተሻለ ውጤት የሚተጉበት ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው ምዘናው የቢ ኤስ እቅድ አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ መካሄዱን ጠቁመው ምዘናውም በዋናነት በተቋማቱ መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር ተቀራራቢ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ታስቦ የሚካሄድ መሆኑን አስረድተዋል።

 

2015. 6ወር  የቢ ኤስ አፈጻጸም ምዘና ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የምዘና መስፈርት ከማዘጋጀት ጀምሮ ለመዛኞች ኦረንቴሽን ተሰጥቶ ወደ ምዘና መገባቱን የትምህርት ቢሮ የእቅድና በጀት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የምዘና ሂደቱን በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸው ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት በተካሄደው ምዘና 469 ተቋማት 590 መዛ ኞች ተመዝነው ለዛሬው የእውቅና መርሀ ግብር መብቃታቸውን አስታውቀዋል።

 

በምዘናው ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1 አጼ ቴውድሮስ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ 2 ረጲ ከኮልፌ ክፍለ ከተማ እንዲሁም 3 ልቤፋና ትምህርት ቤት ከቂርቆስ ክፍለከተማ በመሆን እውቅና ሲሰጣቸው 2 ደረጃ ትምህርት ቤቶች በቢ ኤስ እና 12 ክፍል ውጤት 1 አዲስ ከተማ 2 በሻሌ እንዲሁም ቦሌ አጠቃላይ 2 ደረጃ ትምህርት ቤት 3 በመውጣት እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን በቢኤስ አፈጻጸም ብቻ ደግሞ 1 በላይ ዘለቀ 2 ደረጃ ትምህርት ቤት 2 በሪ 2 ደረጃ እንዲሁም ቤተልሔም 2 ደረጃ ትምህርት ቤት 3 በመሆን ተሸልመዋል።

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

Tuesday, March 21, 2023

የከተማ ግብርና በደጃዝማች ወንድይራድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

 

ቀን 17/7/2015 ዓ.ም

 

የከተማ  ግብርና  በደጃዝማች  ወንድይራድ  የመጀመሪያ ደረጃ  /ቤት

 

በየካ ክፍለ ከተማ  በሚገኘው የደጃች ወንዲራድ  የመጀመሪያ ደረጃ  ትምህርት ቤት የተቀናጀ  የከተማ  ግብርና  በንብ  ማነብና  በእንስሳ ልማት 2 ዙር  የዶሮ እርባታ  25  መምህራንን በማደራጀት ለዘርፉ የሚስፈልገውን  ሳይንሳዊ  ስልጠና  የተግባር የልምድ ልውውጥ እንዲያገኙ በማድረግ  ወደ  ተግባር  ገብቷል፡፡

 

መምህራኑ የመነሻ  ካፒታል አቅም በራሳቸው እዲፈጥሩ በማድረግ  500 ዶሮዎችን በመጀመሪያ ዙር  በት/ቤቱ የዶሮ ማርቢያ ሼድ  እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

 

ከዚህም በተጨማሪ  በት/ቤቱ የከተማ  ግብርና  15 መምህራን  በንብ  ማነብ  ስራ ራሳቸውን አደራጅተው ከአዋኪ ነፃ በሆነ ስፍራ  ከንኪኪ  በራቀ ቦታ ስራ ጀምረዋል፡፡

 

መረጃው የደጃች ወንድይራድ ትምህርት ቤት ነው

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

Thursday, March 16, 2023

በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የትምህርት ብርሀን ምዘና አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

 

ቀን 7/7/2015 .

 

በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የትምህርት ብርሀን ምዘና አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራ እና አጠቃላይ ሱፐር ቪዝን ዳይሬክቶሬት 2015 . የትምህርት ብርሀን ምዘና አተገባበር ዙሪያ ከክፍለከተማና ወረዳ የአፋን ኦሮሞ የጎልማሶች ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

 

የትምህርት ብርሀን ምዘናው በአዲስ አበባ ከተማ 2013 እና 2014. በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ለሁለት ዙር ተካሂዶ 2,000 በላይ ጎልማሶችና ወጣቶች  50% እና ከዚያ በላይ አምጥተው የእውቅና የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራ እና አጠቃላይ ሱፐር ቪዝን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሮቢ ዋሚ አስታውቀዋል፡፡

 

ዳይሬክተሩ አክለውም የዘንድሮው የትምህርት ብርሀን ምዘና ከመጋቢት 11/2015 . ጀምሮ እስከ መጋቢት 30/2015 . ድረስ በሁሉም የጎልማሶች ትምህርት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ጠቁመው በዚህ አመት ከዚህ በፊት ከነበረው የተሻለ ቁጥር ያላቸው ጎልማሶችና ወጣቶችን በአፋን ኦሮሞ  ቋንቋ  በመመዘን ደረጃውን የጠበቀ የእውቅና የምስክር ወረቀት ለመስጠት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱን አስገንዝበዋል፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት  የጎልማሶች ትምህርት ባለሙያው አቶ ጌታቸው በላይነህ በበኩላቸው የትምህርት ብርሀን ምዘናው የማንበብ መጻፍና ማስላት ክህሎቶችን መሰረት አድርጎ እንደሚሰጥ እና 50% እና ከዚያ በላይ የሚያስመዘግቡ ተመዛኞች በመደበኛው ትምህርት 2 ክፍል ካጠናቀቁ ተማሪዎች ጋር አቻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸው አስታውቀዋል፡፡

 

ምዘና ወስደው የሚፈለገውን ማለፊያ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተመዛኞች በመደበኛ ትምህርት 3 ክፍል ገብተው መማር የሚችሉበት እድል ከመመቻቸቱ ባሻገር የተለያዩ የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ገልጸው በምዘናው 50% በታች የሚያስመዘግቡ ጎልማሶችና ወጣቶች በድጋሜ ምዘናውን የሚወስዱበት መንገድ መመቻቸቱንም አስረድተዋል፡፡

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

Ticktack- tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com