ቀን 1/7/2015
ዓ.ም
ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለሚገቡ አዲስ ስልጣኞች የተማሪ ቅበላ ማስጀመሪያ
መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ
ልማት ቢሮዎች በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለሚገቡ አዲስ ስልጣኞች የተማሪ ቅበላ ማስጀመሪያ
መርሃ-ግብር በጋራ አካሄደዋል፡፡
የተማሪ ቅበላ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ
የተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ
ደቻሳ ፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች
፣ የየማስልጠኛ ኮሌጁ ሀላፊዎች ፣ የአሰልጣኞች ሙያ ማህበራት ፣ አስልጣኝ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች
ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የቴክኒክና
ሙያ ስልጠና በተጨባጭ ተግባር የታገዘ በቴክኒክ ትምህርት መስልጠን
ለሚፈልጉ እንዲሁም በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አዳዲስ ክህሎቶችን ማዳበር ለሚፈልጉ ስዎች የሚሰጥ የፈጠራ ክህሎትን ለማስተማር የሚያስችል
ተመራጭ የትምህርት ዘርፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ተማሪዎች በሚፈልጉት የሙያ ዘርፍ እና ደረጃ ላይ መማር የሚችሉ መሆኑን
አመላከተዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው
ዘንድሮ ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ማስልጠኛ ተቋማት ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም
108 የሙያ አይነቶች በ8 ኮሌጆች ስልጠናዎች የሚሰጡ መሆኑን አሳውቀወል፡፡
የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ አስልጣኞች ማህበርን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት
አቶ ትጉ መሀሪ ማህበሩ የመደገፍና የማስተማር ድርሻውን ይወጣል ብለዋል፡፡
በመርሃ-ግበሩ የማስልጠኛ ኮሌጆችም ስራዎች በተሳታፊዎች ተጎብኝተዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
Blog: - https://aacaebc.blogspot.com
You
Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/