Sunday, March 5, 2023

የአሰልጣኞች ስልጠና

 

ቀን 26/6/2015 .

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት በተሻሻለው የስርአተ ጾታ መመሪያ እና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረውን የአሰልጣኞች ስልጠና ማጠናቀቁን አስታወቀ።

 

በስልጠናው የክፍለ ከተማ የዘርፈ ብዙ ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የስነ ዜጋና ስነምግባር መምህራን፣የጋይዳንስና ካውንስሊንግ ባለሙያዎች እንዲሁም የመምህራን ማህበር ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን ሰልጣኞቹም የቀረቡ የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ በቡድን እና በጋራ ውይይት አካሂደዋል።

 

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት  ባለሙያው አቶ ደረጀ ደምሴ በአሰልጣኞች ስልጠና መርሀግብሩ  በአዲስ መልክ ተሻሽሎ በተዘጋጀው  የስርአተ ጾታ ጥቃት መከላከያ መመሪያ ዙሪያ ሰልጣኞች በቂ ግንዛቤ ያገ ኙበትና በቀጣይ በየትምህርት ቤቶቻቸው መመሪያውን መሰረት በማድረግ ለትምህርት ማህበረሰቡ ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችላቸውን ስራ መስራት እንዲችሉ የሚያግዛቸው መሆኑን ጠቁመው በተያያዘ በዚህ ዘመን በርካታ ታዳጊ ወጣቶች ሰለባ እየሆኑበት ባለው ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተገናኘ በሚከሰቱ ጥቃቶች ዙሪያ በዘርፉ ልምድ ባላቸው ባለሙያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን አስረድተዋል።

 

በስልጠናው ኬኒያዊቱዋ የዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የህጻናት የማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት መከላከል አማካሪዋ ሚስ ቤትሪስ ጋቼንጎ ከታዳጊ ህጻናት የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተገናኘ የሚታዩ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተጽእኖዎችን መሰረት ያደረገ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ወላጆችም ሆኑ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ታዳጊ ህጻናት የሚመለከቱዋቸው የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎች እድሜያቸውን ታሳቢ ያደረጉ እና ለተለያዩ ጎጂ ልማዶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

 

በአሰልጣኞች ስልጠናው የተሳተፉ መምህራንም ሆኑ የትምህርት ባለሙያዎች ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ በየትምህርት ቤቶቻቸው ያከናወኗቸው ተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የድጋፍና ክትትል ስራ እንደሚሰራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯ ወይዘሮ አበባ ዘውዴ አስታውቀዋል።

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

Friday, March 3, 2023

ትውልድ ላይ ኢንቨስት በማድረግ ሃገሩን......

በኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር ከቅርብ አመታት ወዲህ በራስ አቅም ከፍተኛ በጀት ተመድቦ እየተተገበረ...

ለበርካታ እናቶች የስራ እድልን ከመፍጠሩም በተጨማሪ ......

የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር መጠነ ማቋረጥን በመቀነስ ጥቅል የትምህርት ተሳትፎ እንዲጨምር ማድረጉን ....

በተሻሻለው የስርዓተ ጾታ መመሪያ እና ተዛማጅ ጉዳዮች

 

ቀን 24/6/2015 .

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት በተሻሻለው የስርዓተ ጾታ መመሪያ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን አሳወቀ።

 

በስልጠናው የክፍለ ከተማ የዘርፈ ብዙ ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የስነ ዜጋና ስነምግባር መምህራን እና የጋይዳንስና ካውንስሊንግ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

 

በስልጠናው መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ዘውዴ እንዳስታወቁት የስርዓተ ጾታ መመሪያው 2007 . በኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስተር ተዘጋጅቶ በየትምህርት ተቋማቱ ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመው መመሪያው ዳግም በአዲስ መልክ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ አድርጎ በመዘጋጀቱ በዚህ የአሰልጣ ኞች ስልጠና ተሳታፊ የሆኑ መምህራንም ሆኑ የትምህርት ባለሙያዎች በየትምህርት ቤቶቻቸው መመሪያውን መሰረት በማድረግ ለትምህርት ማህበረሰቡ ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ባለሙያ አቶ ደረጀ ደምሴ በመርሀ ግብሩ ጾታዊ ጥቃትንም ሆነ በህጻናት ላይ የሚደርሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል የወጡ አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የህግ ማእቀፎችን መሰረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ሰልጣኞቹም በቀረቡ የመወያያ ሀሳቦች ዙሪያ በቡድንና በጋራ ውይይት አድርገዋል።

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

Wednesday, March 1, 2023

ማስታወቂያ!

 

ቀን 22/6/2015 .

 

የተማሪዎች ምገባ ክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ መደብ ላይ ተወዳድራችሁ ያለፋችሁ ተወዳዳሪዎች ስማችሁን ከታች ባለው ሊንክ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከእሮብ ማለትም ከ29/6/2015 ዓ.ም ጀምሮ በየተመደባችሁበት ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት በአካል በመሄድ ምደባችሁን እንድትወስዱ እናሳውቃለን፡፡

 

https://aacaebc.wordpress.com/2023/03/01/ቀን-22-6-2015-ዓ-ም/

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

የ6ወር የቢ ኤስ ሲ እቅድ አፈጻጸም ምዘና

 

ቀን 22/6/2015 .

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት በትምህርት ተቋማት ሲያካሂድ የቆየውን 2015 . 6ወር የቢ ኤስ እቅድ አፈጻጸም ምዘና በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡

 

ምዘናው በሁሉም የመንግስት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጨምሮ በክፍለከተማ እና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች አስሩን ዋና ዋና ግቦች መነሻ በማድረግ የተካሄደ ሲሆን ቀደም ሲል ምዘናውን ለሚያካሂዱ 400 በላይ ለሚሆኑ መዛኞችና አስተባባሪዎች ኦረንቴሽን መሰጠቱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ጌታሁን ለማ ገልጸዋል፡፡ 

 

በትምህርት ተቋማት የሚካሄደው የቢ ኤስ እቅድ አፈጻጸም ምዘና ተቋማቱ ያሉበትን ሁኔታ በማወቅ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ከማስቻሉ ባሻገር በተቋማቱ መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት  እንዲችሉ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመው ምዘናው ያለምንም እንከን እንዲካሄድ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ መዛኞችና ተመዛኝ  ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/