Tuesday, March 7, 2023

በአዲስ አበባ ከተማ የተማሪዎች ውጤትን ለማሻሻል የሚያስችል የዋንጫ ርክክብ ተካሄደ።

 

ቀን 28/6/2015 .

 

በአዲስ አበባ ከተማ የተማሪዎች ውጤትን ለማሻሻል የሚያስችል የዋንጫ ርክክብ ተካሄደ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ ከተማ አቀፍ እና ሀገራቀፍ ፈተና ተፈታኝ የሆ ኑ የ6ኛ ፣የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት የላቀ እንዲሆን እና ተማሪዎች በፍክክር መንፈስ የተሻለ ውጤት መስመዝገብ እንዲችሉ የተማሪዎች ውጤት ማሻሻያ የዋንጫ ርክክብ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄዳል፡፡

 

ዋንጫው ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት /ቤት ርክክብ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በሁሉም ክፍለከተሞችና በሁሉም ትምህርት ቤቶች  የሚዘዋወር ይሆናል።

 

ዋንጫው 6 8 እና 12 ክፍል ሀገር አቀፍና ከተማ አቀፍ ፈተናዎች ላይ የሚኖረውን ውጤት ለማሻሻል እንዲቻል በተማሪዎች ላይ መነቃቃትንና የውድድር መንፈስን ለማሳደግ  ትኩረት ተሰጦ የሚሰራበት ነው።

 

መድረኩ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዘጋጅነት በፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጀመረ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል ፣ የቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊ ሳምራዊት ቅባቱ ፣ ርዕሳነ መምህራን ፣ ባለሙያዎች ፣ ወላጆች ፣ መምህራን እና ተማሪዎች ተሳታፊ ሁነዋል፡፡

 

በመድረኩ በ2015 የትምህርት ዘመን ከተማ አቀፍ እና ሀገራቀፍ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በፍክክር መንፈስ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ በሶስቱም የክፍል ደረጃዎች ላይ ተማሪዎች ተግተው እንዲሰሩ እንደሚያደርግ የተመላከተ ሲሆን በዓመቱ መጨረሺያ ላይ ዋንጫዎቹ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ላሉባቸው ክፍለ ከተማዎች የሚበረከቱ እንደሚሆኑ ተገልጻል፡፡

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

Sunday, March 5, 2023

የአሰልጣኞች ስልጠና

 

ቀን 26/6/2015 .

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት በተሻሻለው የስርአተ ጾታ መመሪያ እና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረውን የአሰልጣኞች ስልጠና ማጠናቀቁን አስታወቀ።

 

በስልጠናው የክፍለ ከተማ የዘርፈ ብዙ ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የስነ ዜጋና ስነምግባር መምህራን፣የጋይዳንስና ካውንስሊንግ ባለሙያዎች እንዲሁም የመምህራን ማህበር ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን ሰልጣኞቹም የቀረቡ የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ በቡድን እና በጋራ ውይይት አካሂደዋል።

 

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት  ባለሙያው አቶ ደረጀ ደምሴ በአሰልጣኞች ስልጠና መርሀግብሩ  በአዲስ መልክ ተሻሽሎ በተዘጋጀው  የስርአተ ጾታ ጥቃት መከላከያ መመሪያ ዙሪያ ሰልጣኞች በቂ ግንዛቤ ያገ ኙበትና በቀጣይ በየትምህርት ቤቶቻቸው መመሪያውን መሰረት በማድረግ ለትምህርት ማህበረሰቡ ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችላቸውን ስራ መስራት እንዲችሉ የሚያግዛቸው መሆኑን ጠቁመው በተያያዘ በዚህ ዘመን በርካታ ታዳጊ ወጣቶች ሰለባ እየሆኑበት ባለው ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተገናኘ በሚከሰቱ ጥቃቶች ዙሪያ በዘርፉ ልምድ ባላቸው ባለሙያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን አስረድተዋል።

 

በስልጠናው ኬኒያዊቱዋ የዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የህጻናት የማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት መከላከል አማካሪዋ ሚስ ቤትሪስ ጋቼንጎ ከታዳጊ ህጻናት የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተገናኘ የሚታዩ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተጽእኖዎችን መሰረት ያደረገ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ወላጆችም ሆኑ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ታዳጊ ህጻናት የሚመለከቱዋቸው የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎች እድሜያቸውን ታሳቢ ያደረጉ እና ለተለያዩ ጎጂ ልማዶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

 

በአሰልጣኞች ስልጠናው የተሳተፉ መምህራንም ሆኑ የትምህርት ባለሙያዎች ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ በየትምህርት ቤቶቻቸው ያከናወኗቸው ተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የድጋፍና ክትትል ስራ እንደሚሰራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯ ወይዘሮ አበባ ዘውዴ አስታውቀዋል።

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/