Thursday, February 23, 2023

ትምህርት በሬዲዮ

 

ቀን 17/6/2015 .

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015 የትምህርት ዘመን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት ያዘጋጃቸውን የትምህርት በሬዲዮኖች በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ሁሉም የግል ፣ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከቢሮ የቴሌግራም ገጽ

https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

ላይ በመውስድ ለመማር ማስተማር ስራው እገዛ እንዲያደርግ እና ለተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆን እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

 Blog: - https://aacaebc.blogspot.com

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ቀደም ሲል ሴክተሩን በአመራርነት አገልግለው ወደ ሌላ ዘርፍ ለሄዱ አመራሮች የሽኝት መርሀ ግብር አካሄደ፡፡

 

ቀን 16/6/2015 .

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ቀደም ሲል ሴክተሩን በአመራርነት አገልግለው ወደ ሌላ ዘርፍ ለሄዱ አመራሮች የሽኝት መርሀ ግብር አካሄደ፡፡

 

ሽኝቱ የተደረገላቸው ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በምክትል ቢሮ ኃላፊነት ሲያገለግሉ ለነበሩት ለአቶ ሳመሶን መለሰ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ ለቆዩት አቶ አለልኝ ወልዴ ሲሆን በሽኝት መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የማኔጅመንት እና የፕሮሰስ ካውንስል አባላትን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በሽኝት ፕሮግራሙ ባስተላለፉት መልዕክት በዛሬው እለት የሚሸኙት አመራሮች በትምህርት ሴክተሩ በነበራቸው ቆይታ በሴክተሩ ለተመዘገበው ውጤት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው አሁን በተመደቡበት ዘርፍም ለትምህርት ሴከክተሩ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነታቸው መሆኑን በመግለጽ በተመደቡበት ሴክተር መልካም እድል እንዲገጥማቸውና በስራቸውም ውጤታማ እንዲሆኑ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

ሽኝቱ የተደረገላቸው አቶ ሳምሶን መለሰ እና አቶ አለልኝ ወልዴ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና በክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ለተደረገላቸው የክብር ሽኝት ላቅ ያለ ምስጋና  በማቅረብ በትምህርት ሴክተሩ በነበራቸው ቆይታ ያካበቱት የስራ ልምድም ሆነ በጋራ የመስራት ባህል አሁን በተመደቡበት ሴክተር ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዛቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 

 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

 

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ...

 

TikTok- tiktok.com/@aaeducationbureau

 

Telegram https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

 

Twitter https://twitter.com/aacaebc

 

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

 

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

 

Website: - aaceb.gov.et

 

Email;- aacaebc@gmail.com

 

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/

Wednesday, June 22, 2016

Transfer Policy 2007

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2007 ዓ.ም የመጀመርያ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች  የተማሪዎች ከክፍል ወደ ክፍል የዝውውር ፖሊሲ


Tuesday, June 21, 2016

ክብርና ምስጋና ለህዳሴው ትውልድ አናፂ መምህራን






በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  የመምህራን ዕውቅናና ስነ-ስርዓት  ሰኔ 2008 ዓ.ም


Monday, June 20, 2016

Photo Gallery : Teacher Certification Program and Thanks giving























Tuesday, April 12, 2016



ቀን 03/08/2008 ዓ.ም

6ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ፌስቲቫል ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 6ተኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ፌስቲቫል “ጥራት ያለው ትምህርት ለዘላቂ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን” በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 29-ሚያዝያ 02/2008 ዓ.ም በዳግማዊ ሚኒሊክ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በድምቀት አካሄደ፡፡
በፌስቲቫሉ መክፈቻ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲላሞ ኦቶሬ እንዳስታወቁት የትምህርት ፌስቲቫሉ የተሻለ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር የትምህርት ማህበረሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልፀው ፌስቲቫሉ የተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታና የምርምር አድማስ በማስፋትና በዚህም ሂደት የተገኙ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን ለህብረተሰቡ እንዲሁም ለትምህርት ተቋማት እንዲስፋፉ በማድረግ ለቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚያስችል አስገንዝበዋል፡፡ 
ኃላፊው አክለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፌስቲቫሉን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ በቢሮ ደረጃ ኮሚቴዎችን በማዋቀር የቢሮውን አቅም በማቀናጀትና በተደራጀ መልኩ በመጠቀም ፌስቲቫሉን የተሳካ እንዲሆን ያደረገው ተነሳሽነት አበረታች መሆኑን ጠቅሰው መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ለሚሰራቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች መሳካት ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ኃላፊነት ስላለባቸው ብቁ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ የሳይንስና ሒሳብ ትምህርት ዘርፍ የተፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ሁሉም የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ፌስቲቫሉ ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ ከ10ሩ ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የልዑካን ቡድኖች የሽብርቅ ስራዎቻቸውን ለዕይታ ያበቁ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን በተማሪዎች የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች በተለያዩ አካላት እንዲጎበኙ ከመደረጉ ባሻገር ፌስቲቫሉን ምክንያት በማድረግ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር፣ ትምህርታዊ አውደ ጥናት እንዲሁም በተማሪዎች መካከል የስነ-ፅሁፍ ውድድሮች ተካሄደዋል፡፡
በፌስቲቫሉ ማጠቃለያ በየዘርፉ አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎችና ክፍለ ከተሞች የገንዘብና የዋንጫ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በየትምህርት እርከኑ በተፈጥሮና በማህበራዊ ሳይንስ የፈጠራ ስራ አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎች ከ2,500-3,500 ብር ሽልማት ሲያገኙ በፌስቲቫሉ የነቃ ተሳትፎ በማድረግና በአጠቃላይ ውጤት 1ኛ አራዳ 2ኛ ቦሌ እንዲሁም 3ኛ የካ ክፍለ ከተማ በመሆን  የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
 ዘገባው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዬች ደጋፊ የሥራ ሂደት ነው፡፡