Wednesday, June 22, 2016
Tuesday, June 21, 2016
Monday, June 20, 2016
Tuesday, April 12, 2016
ቀን 03/08/2008 ዓ.ም
6ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ፌስቲቫል ተካሄደ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 6ተኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ፌስቲቫል “ጥራት ያለው ትምህርት ለዘላቂ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን” በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 29-ሚያዝያ 02/2008 ዓ.ም በዳግማዊ ሚኒሊክ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በድምቀት አካሄደ፡፡
በፌስቲቫሉ መክፈቻ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲላሞ ኦቶሬ እንዳስታወቁት የትምህርት ፌስቲቫሉ የተሻለ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር የትምህርት ማህበረሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልፀው ፌስቲቫሉ የተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታና የምርምር አድማስ በማስፋትና በዚህም ሂደት የተገኙ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን ለህብረተሰቡ እንዲሁም ለትምህርት ተቋማት እንዲስፋፉ በማድረግ ለቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚያስችል አስገንዝበዋል፡፡
ኃላፊው አክለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፌስቲቫሉን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ በቢሮ ደረጃ ኮሚቴዎችን በማዋቀር የቢሮውን አቅም በማቀናጀትና በተደራጀ መልኩ በመጠቀም ፌስቲቫሉን የተሳካ እንዲሆን ያደረገው ተነሳሽነት አበረታች መሆኑን ጠቅሰው መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ለሚሰራቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች መሳካት ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ኃላፊነት ስላለባቸው ብቁ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ የሳይንስና ሒሳብ ትምህርት ዘርፍ የተፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ሁሉም የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ፌስቲቫሉ ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ ከ10ሩ ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የልዑካን ቡድኖች የሽብርቅ ስራዎቻቸውን ለዕይታ ያበቁ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን በተማሪዎች የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች በተለያዩ አካላት እንዲጎበኙ ከመደረጉ ባሻገር ፌስቲቫሉን ምክንያት በማድረግ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር፣ ትምህርታዊ አውደ ጥናት እንዲሁም በተማሪዎች መካከል የስነ-ፅሁፍ ውድድሮች ተካሄደዋል፡፡
በፌስቲቫሉ ማጠቃለያ በየዘርፉ አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎችና ክፍለ ከተሞች የገንዘብና የዋንጫ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በየትምህርት እርከኑ በተፈጥሮና በማህበራዊ ሳይንስ የፈጠራ ስራ አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎች ከ2,500-3,500 ብር ሽልማት ሲያገኙ በፌስቲቫሉ የነቃ ተሳትፎ በማድረግና በአጠቃላይ ውጤት 1ኛ አራዳ 2ኛ ቦሌ እንዲሁም 3ኛ የካ ክፍለ ከተማ በመሆን የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ዘገባው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዬች ደጋፊ የሥራ ሂደት ነው፡፡
Thursday, March 31, 2016
10 ኪሎ ሜትር የተማሪዎች ሩጫ ውድድር ተካሄደ
መጋቢት
19/7/2008 ዓ/ም
1.
በውድድሩም የቡድን የዋንጫ አሸናፊ ፡- በወንዶች
1ኛ የዋንጫ ተሸላሚ
የካ ክፍለ ከተማ በ 11 ነጥብ
2ኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ
በ 25 ነጥብ
3ኛ ጉለሌ ክፍለ ከተማ
በ 33 ነጥብ
በሴቶች
1ኛ የዋንጫ ተሸላሚ
ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በ 15 ነጥብ
2ኛ የካ
ክፍለ ከተማ በ 33 ነጥብ
3ኛ ቂርቆስ ክፍለ
ከተማ በ 50 ነጥብ
2.
ብቸኛ የክራንች ተወዳዳሪ ፡-
ተማሪ ንጉስነህ መኮንን
ከነሻሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት /ቦሌ ክፍለከተማ
3. በሩጫ ውድድሩ የቦንድ ተሸላሚዎች ፡-
በወንዶች 1ኛ ተማሪ ግዛቸው ተካ ከየካ ክፍለከተማ ከበበዮት ቅርስ ት/ቤት
2ኛ ተማሪ አሠፋ
ጌጤ ከንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ
ከነጻነት
ጮራ ት/ቤት
3ኛ ተማሪ ተሸመ ጉዲሣ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ከአየር አንባ ት/ቤት
4ኛ አብደላ ሰማ ከየካ ክፍለከተማ ከከፍተኛ 12 ት/ቤት
በሴቶች 1ኛ ተማሪ ገነት መኩረያ ከአራዳ ክፍለ
ከተማ ከመስከረም
2ኛ ደረጃ ት/ቤት
2ኛ እቴነሽ አብዴሳ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ
ከንፋስ ስልክ ላፍቶ 2ኛ
ደረጃ ት/ቤት
3ኛ ትርሃስ ገብረህይወት
ከኮልፌ ክፍለከተማ ከአየር ጤና 2ኛ
ደረጃ ት/ቤት
4ኛ ተማሪ ምህረት ግዛው ከኮልፌ ክፍለከተማ ከ ቃሌ
የመጀመሪያ
ደረጃ ት/ቤት
4.
በሩጫ ውድድሩ በቡድን የቦንድ ተሸላሚዎች ፡-
በወንዶች የካ ክፍለ ከተማ
በ 11 ነጥብ
በሴቶች ኮልፌ
ቀራኒዪ ክፍለ ከተማ በ 15 ነጥብ ሆነዋል፡፡
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለነበረው ንቁ ተሳትፍ ከአ/አ ታላቁ ሀዳሴ ግድብ ግንባታ አስተባባሪ ጽ/ቤት ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)